Yem Bor Mountain - camping adventure
No image available
Experience Details
- When: October 26, 2025 12:00 AM
- Price: ETB Call for Price / person
- Category: Outdoors
About this Experience
ይህ ጉዞ በፍፁም እንዳያመልጣችሁ! 🏔️🏕️
ጥቅምት 16 እና 17 - የሳሞ ኤታ በዓል በየም ምድር ፤ ቦር ተራራ ላይ
ከእኛ ጋር ለመጓዝ ዝግጅ ናችሁ?
🗓️ ጥቅምት 16 እና 17 (እሁድ እና ሰኞ)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኘው የም ብሔረሰብ ለጥቅምት ወር ልዩ ሥፍራን ይሰጣል፡፡ ኅብረተሰቡ የጥቅምት ወር አጋማሽ እንዳለፈ ቦር ተራራ ላይ፣ የባህላዊ መድኃኒት ለቀማን ከልሂቅ እስከ ደቂቅ የሚሳተፍበትን ኩነት ያደርጋል ፡፡ ‹‹”ሳሞ ኤታ”››
”ሳሞ ኤታ” በየዓመቱ ጥቅምት 17 ቀን “ቦር”በሚባል ተራራ ላይ የባህላዊ መድኃኒቶች ለቀማ ይካሄዳል፡፡
”ሳሞ ኤታ” ማለት የከረመ መድኃኒት ማለት ነው፡፡
በቦር ተራራ የሚገኙ ዕፅዋት ለሰው ብቻ ሳይሆኑ ለእንሰሳትም እንደሚያገለግሉ በኅብረተሰቡ ይታመናል፡፡
የዓመት የመድኃኒት አስቤዛ ጥቅምት 17 ይሰበሰባል፡፡ “የም” በዕፅዋት ጥበብ አስቀድሞ በሽታን ይከላከላል፡፡ ቀጥሎም ሕመምን ያስወግዳል፡፡ ፈውስን ከምድር ገጸ በረከት የሚያገኝ ጥበበኛ ሕዝብ ነው፡:
በዚህ ዕለት የአካባቢው ነዋሪዎች በተራራው ላይ ካሉ በርካታ የእፅዋት አይነቶች ቅጠላቸውን፣ ስሮቻቸውን እና ቅርፊታቸውን በመሰብሰብ ቤታቸው ወስደው በአግባቡ በማዘጋጀት ለሰውና ለእንስሳት የሚሆን መድሃኒትነት ይቀምሙበታል፡፡
እኛ አስደናቂውን የየም ህዝብ ባህል ፣ ታሪክ ፣ ቋንቋ እና ቅርስ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ ተፈጥሯዊ የቱሪዝም መስህቦችን ዘንድሮም ለመጎብኘት ተዘጋጅተናል!
ለምዝገባና ተጨማሪ መረጃዎች በተከታዮቹ አድራሻዎች ብቻ ታገኙናላችሁ!
+251942545470 , +251964423971
አስቀድሞ ቦታ በማስያዝ የክፍያ ቅናሽ እድሉን ይጠቀሙ!
Reviews
You must be logged in to leave a review. Login here
No reviews yet. Be the first to leave one!